Fana: At a Speed of Life!

የሰው እገታ የፈፀመው ተከሳሽ በ18 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰው እገታ የፈፀመው ተከሳሽ በ18 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱን የምዕራብ ጎንደር ዞን ፍርድ ቤት ገለጸ፡፡
ተከሳሽ ፈለቀ ተሰራ የተባለ ግለሰብ በፈፀሙት የህፃን ጠለፋ ወንጀል ተጠርጥሮ ታህሳስ 18 ቀን 2014ዓ.ም በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ÷በፈፀመው የህፃን ጠለፋ ድርጊትም በከባድ ወንጀል ክስ የተመሰረተበት መሆኑ ተገልጿል፡፡
የምዕራብ ጎንደር ዞን ፍርድ ቤት የካቲት 12 ቀን 2014ዓ.ም በዋለው ችሎት ወንጀለኛውን ያስጠነቅቃል ሌሎችንም ያስተምራል ያለውን የ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.