በሐረሪ ክልል ባለፉት 6 ወራት 580 ሚሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት 580 ሚሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡ ተገለፀ፡፡
የሐረሪ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን ቢሮ የ2014 በጀት አመት የ6 ወር ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ለክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ቀርቧል፡፡
በዚህም ግብር ከፋዮች ላይ አስፈላጊ ክትትልና ቁጥጥር በማካሄድ 25 የግብር ስወራ ታክስን ለማጋለጥ ታቅዶ ሙሉ በሙሉ መስራት መቻሉ የተጠቀሰ ሲሆን ÷ በ6 ወራት ውስጥ 352 የሽያጭ መመዝገቢያ ምርመራና ቁጥጥር ለማድረግ ታቅዶ መቶ በመቶ ለማከናወን መቻሉም ተገልጿል፡፡
በ6 ወራት ውስጥ 593 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 580 ሚሊየን ወይም የእቅዱን 98 በመቶ ማሳካት ተችሏል ነው የተባለው፡፡
ገቢው ካለፈው አመት 6 ወር አፈፃጸም ጋር ሲነፃፀር በ211 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ወይም 58 በመቶ ብልጫ እንዳለው ታውቋል፡፡
በክልሉ 2014 በጀት አመት በግብር ታክስና ማዘጋጃ ቤታዊ ገቢን ጨምሮ በአጠቃላይ 1 ነጥብ 64 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!