የዓለም የኩላሊት ቀን በነፃ የኩላሊት ምርመራ ህክምና አገልግሎት በመስጠት እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የኩላሊት ቀን በተለያዩ ከተሞች በነፃ የኩላሊት ምርመራ ህክምና አገልግሎት በመስጠት እየተከበረ ነው።
በኢትዮጵያ አሁን ላይ ወደ 10 ሚሊየን የሚጠጉ የኩላሊት ህሙማን እንዳሉ ግምታዊ መረጃዎች ያሳያሉ መባሉን ኢቢሲ ዘግቧል።
በየጊዜው የበሽታው ስርጭት እየጨመረ ሲሆን÷ለዚህም የተዛባ የአመጋገብ ሥርዓት፣ የስኳር በሽታ እና የመሳሰሉት ለበሽታው መጨመር ጉልህ ድርሻ እንዳላቸው ተገልጿል።
በሽታው ላይ መከላከልን መሰረት ያደረገ ስራ በመንግስት እና በማህበራት በኩል እየተከናወነ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን÷ የዓለም የኩላሊት ቀንም በየዓመቱ በነፃ ምርመራ እየተከበረ ይገኛል።
የነፃ ምርመራው ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ ብሔራዊ ቴአትር፣ ሸጎሌ፣ አዲሱ ገበያ እና ሳሪስ ጤና ጣቢያዎች እንዲሁም በክልል ጎንደር፣ ሀዋሳ፣ ድሬዳዋ እና አዳማ ከተሞች እየተሰጠ ነው ሲል የኢትዮጵያ የኩላሊት ህሙማን ማህበር ገልጿል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!