Fana: At a Speed of Life!

የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በአፍሪካ ቀንድ ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 85 ሚሊየን ዶላር ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በአፍሪካ ቀንድ ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 85 ሚሊየን ዶላር ይፋ አደረገች።
 
ድጋፉ በዋናነት በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል ሲሆን፥ በዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ በቀይ መስቀል፣ በዩኒሴፍ እና በተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አማካኝነት የሚተገበር መሆኑን የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ጸሃፊና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፍትስ ገልጸዋል።
 
የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን፥ የአየር ንበረት ለውጥ ተፅዕኖ በቀጠናው ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ እንዳባባሰው ገልጸዋል።
 
ዛሬ ይፋ የሆነው ድጋፍም ሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ኤጀንሲዎች አስቸኳይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል ማለታቸውን ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.