Fana: At a Speed of Life!

ዲፕሎማቶችና የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ማኅበር ተወካዮች በሊባኖስ እሥር ቤቶች የሚገኙ ዜጎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤሩት የሚገኘው የኢፌዴሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ዲፕሎማቶችና የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ማኅበር ተወካዮች በሊባኖስ በተለያዩ እሥር ቤቶች የሚገኙ ዜጎችን ጎብኝተዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ በትሪፖሊ፣ በባብዳ፣ በቨርዳን እና በዛህሌ የሚገኙ ሴት ኢትዮጵያዊ ዜጎችን መጎብኘት መቻሉ ተመላክቷል፡፡
ልዑካን ቡድኑ በጉብኝታቸው ከታራሚዎች እና ከእሥር ቤቶቹ ዋና ኃላፊዎች ጋር በታራሚ ዜጎች አያያዝ ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በእሥር ቤቱ ብዙ ጊዜ የቆዩትንና ለፍርድ ያልቀረቡት ኢትዮጵያውያን ታራሚዎች እንዲሁም ፍርድ ቤት ቀርበው ውሳኔ ያላገኙትንና ጠበቃ የሌላቸውን በማንሳት ምክክር ተደርጓል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሻሻሎች ቢኖሩም ባለፈዉ ዓመት በኮቪድ-19 እና በሊባኖስ በተከሰተው የፖለቲካ አለመረጋጋት በርካታ ፍርድ ቤቶች ዝግ ሆነው መቆየታቸውን እና አንዳንድ ጠበቆች ጉዳዩን ከያዙ በኋላ ተመልሰው አለማየት እና የአስተርጓሚ ችግሮች እንደነበሩ ኃላፊዎቹ አንስተዋል።
ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤቱ በበኩሉ የአስተርጓሚ ጥያቄ በጠበቃቸው ወይም በፖሊስ በኩል ሲቀርብ አስፈላጊውን ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን፣ በጠበቆች በኩል ለተነሳው ጉዳይ ነጻ ድጋፍ የሚያደርጉ የህግ አካላት በመኖራቸው ማሳተፍ እንደሚቻል ጠቁሟል፡፡
አንዳንድ በከባድ ወንጀል የተመዘገቡ ፋይሎችን ረጅም ጊዜ የቆዩና የሚታወቁ ስለሆነ በሥልክም ቢሆን ጠበቆችን በማግኘት ጉዳዩን እንደሚከታተል ነው የገለጸው፡፡
በጉብኝቱ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቷቸው ድጋፍና ክትትል የሚሹ ዜጎች መለየታቸውን በቤሩት ከኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.