Fana: At a Speed of Life!

የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ከመጋቢት 5 ቀን ጀምሮ የመማር ማስተማር ሥራውን ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ቡድን ውድመት ደርሶበት የነበረው የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ከመጋቢት 5 ቀን ጀምሮ ከ3 ሺህ 600 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማር ሥራውን እንደሚቀጥል ገለጸ።

የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ሱልጣን መሀመድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ከሽብር ቡድኑ ውድመት በኋላ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል።

በዚህም ተማሪዎች መጋቢት 5 እና 6 ቀን ማለትም የፊታችን ሰኞና ማክሰኞ ወደ ግቢያቸው መምጣት ይችላሉ ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ የቅበላ መርሃ-ግብሩ የ2013 ዓ.ም የመጀመሪያ ዓመት የሆኑ ከ3 ሺህ 600 በላይ ተማሪዎችን እንደሚቀበል ዶክተር ሱልጣን ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለትም የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ጨምሮ ሁሉም የተቋሙ ሠራተኞች የጽዳት ፕሮግራም ማካሄዳቸው የተገለጸ ሲሆን ከተቋሙ ከከተማ አስተዳደሩና ከሚመለከታቸው አካላት የቅበላ ኮሚቴ ተቋቋሞ የተሳካ ቅበላ ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁ ነው የተነገረው።

ዩኒቨርሲቲው ከ6 ቢሊየን ብር በላይ በሽብር ቡድኑ ውድመት እንደደረሰበት የተናገሩት ዶክተር ሱልጣን ከደጋፊ አካላት ከ47 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መገኘቱንም ገልጸዋል።

በከድር መሀመድ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.