Fana: At a Speed of Life!

ፓርቲው በጉባዔው የሰላምና የኑሮ ውድነት ላይ የመፍትሄ አቅጣጫ ያስቀምጣል ብለን እንጠብቃለን – የመዲናዋ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ብልጽግና ፓርቲ በጉባዔው በተለይም የሰላም ጉዳይና የኑሮ ውድነት ላይ በጥልቀት መክሮ የመፍትሄ አቅጣጫ ያስቀምጣል ብለን እንጠብቃለን ሲሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በአሁኑ ወቅት በተለይም የምግብ ፍጆታ ጉዳይ ከባድ ፈተና ሆኖብናል ብለዋል።
የሸቀጦች ዋጋ መናር፣ በዓለም ላይ የሚስተዋለውን የሰላምና መረጋጋት እጦት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ እየናረ መምጣትና የዘይት ዋጋ ማሻቀብም የተደራረበ ችግር እያስከተለ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የመልካም አስተዳደር ችግር፣ የሰላም ጉዳይ፣ ሌብነት፣ ዘረፋና የህገ ወጦች መበራከትም ህዝብን ለእንግልትና ችግር እየዳረገ መሆኑን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
እነዚህና ሌሎች አገራዊ ችግሮች ባሉበት ወቅት ጉባኤውን የሚያካሂደው ገዥው ፓርቲ ብልጽግና በተለይም በኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት ላይ በጥልቀት መክሮ ጊዜያዊና ዘላቂ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ብለን እንጠብቃለን ብለዋል።
ከዚህ ባለፈም ለወጣቶች የስራ አድል ፈጠራ መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባልም ነው ያሉት።
የብልጽግና ፓርቲ በጉባኤው በጥልቀት መክሮ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ሊያሸጋግር የሚችል ውሳኔ ያሳልፋል የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ነው ነዋሪዎቹ ለኢዜአ የገለጹት።
የብልጽግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ ከነገ ጀምሮ ለሶስት ቀናት በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን÷ በጉባዔው ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ተነስተው ለመፍትሄው አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.