Fana: At a Speed of Life!

የጣና በለስ ቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካ መደበኛ ነጭ ስኳር የማምረት ሥራውን ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣና በለስ ቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካ የቴስቲንግና ኮሚሽኒንግ ሥራዎች ተከናውነውና ቀሪ የማስተካከያ ሥራዎቹ ተጠናቀው ዛሬ መደበኛ ነጭ ስኳር የማምረት ሥራውን ጀመረ፡፡

ምርት የማምረት ስራውን ያስጀመሩት የፋብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አንተነህ አሰጌ እንደገለጹት÷ ፋብሪካው በዚህ ዓመት ከ150 ሺህ እስከ 200 ሺህ ኩንታል ስኳር ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፋብሪካው በሙሉ የዲዛይን አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ በቀን 12ሺህ ቶን ሸንኮራ አገዳ በመፍጨት በቀን ከ9 እስከ 10 ሺህ ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም ይኖረዋል ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም 45 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ በማምረት 17 ነጥብ 5 ሜጋ ዋት ለፋብሪካው ማንቀሳቀሻ በመጠቀም ቀሪውን የኤሌክትሪክ መጠን በመሸጥ ተጨማሪ ገቢ ያስገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም አስረድተዋል።

ሞላሰስና ሌሎች ተረፈ ምርቶችን በመሸጥም ገቢውን ያሳድጋል ማለታቸውን ከስኳር ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ለ20 ሺህ ዜጎች ቋሚ፣ ኮንትራት እና ጊዜያዊ የስራ ዕድል የሚፈጥር ሲሆን÷ የበለስ ስኳር ፋብሪካ ግንቦት 29 ቀን 2013 ዓ.ም የሙከራ ምርት በማምረት መመረቁ ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.