Fana: At a Speed of Life!

በብልፅግና ፓርቲ ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ ለመታደም የደቡብ ሱዳን እህት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ከነገ ጀምሮ በሚያደርገው አንደኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ ለመታደም የደቡብ ሱዳን ህዝቦች ነጻነት ግንባር ምክትል ሊቀመንበር እና የአገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት በዶክተር ጀምስ ዋኒ ኢጋ የተመራው ልዑክ አዲስ አበባ ገብቷል።
የልዑካን ቡድኑ አዲስ አበባ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ አምባሳደር አብዱልቃድር በረከት አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.