በኢትዮጵያ የፀሃይ ሃይል ፓርክን ማስፋፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ ከዓለም አቀፉ ታዳሽ የፀሃይ ኃይል ኅብረት ልዑካን ቡድን ጋር መከሩ፡፡
አምባሳደር ትዝታ ኅብረቱ በኢትዮጵያ ከሚፈጽመው ተልዕኮ ጋር በተገናኘ ከልዑካን ቡድኑ ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡
ታዳሽ የፀሃይ ኃይልን በኢትዮጵያ በመጠቀም ውሃ ለመግፋት እና የአገልግሎት ሥርዓቱን ለማሻሻል ብሎም ታዳሽ የፀሃይ ኃይል ፓርክ በኢትዮጵያ ማስፋት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡