Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግና ፓርቲ በሚያደርገው አንደኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ ለመታደም የኡጋንዳና ቱርክ እህት ፓርቲዎች ልዑካን አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ በሚያደርገው አንደኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ ለመታደም የኡጋንዳና ቱርክ እህት ፓርቲዎች ልዑካን አዲስ አበባ ገብተዋል።

ከዛሬ ጀምሮ በሚደርገው አንደኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ ለመታደም የኡጋንዳው ናሽናል ሬሲስታንስ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አለፐር ሳይመን የሚመሩት ልዑክ አዲስ አበባ ገብቷል።

የፓርቲውን የውጭ ግኑኝነት ዳይሬክተርና የስራ አሰፈፃሚ ኮሚቴ አባላቶችንም ያቀፈው የልዑካን ቡድኑ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ፍሰሀ ሻውል አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በተመሳሳይ ለብልፅግና ፓርቲ አንደኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ የቱርኩ ኤ ኬ ፒ ፓርቲ የውጭ ጉዳዮች ምክትል ሊቀመንበር ፌቭዚ ሻንቨርዲ የሚመሩት የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል።

የልዑካን ቡድኑ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አውሮፓና አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አማባሳደር እሸቴ ጥላሁን አቀባበል እንዳደረጉለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.