የዶኔስክ ሪፐብሊክ ኃይሎች የዩክሬኗን የቮልኖቫካ ከተማ ተቆጣጠሩ
አዲስ አበባ፣መጋቢት 2፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዶኔስክ ሪፐብሊክ ኃይሎች የዩክሬኗን የቮልኖቫካ ከተማ መቆጣጠራቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢጎር ኮናሼንኮቭ እንደገለፁት የዶኔትስክ ሪፐብሊክ ሃይሎች ቡድን የቮልኖቫካ ከተማን የተቆጣጠረ ሲሆን በአካባቢው የሚገኙትን የኦልጊንካ፣ ቬሊኮ-አናዶል፣ ዘሌኒ ጋይ ስፍራዎችንም መቆጣጠር መቻሉን ገልፀዋል።
የዶኔስክ ሪፐብሊክ የህዝቡ ታጣቂዎች በተጨማሪም በማሪፖል ከተማ ዙሪያ ያለውን ከበባ እያጠናከሩ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረች ወዲህ የዶኔስክ እና የሉጋኔስክ ሪፐብሊክ ሚሊሻዎች በዶንባስ በሚካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ በከፍተኛ ደረጃ እየተሳተፉ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት የሩስያ ጦር የማጥቃት እንቅስቃሴውን የቀጠለ ሲሆን ፔትሮቭስኮዬ፣ኢቭጌኖቭካ፣ኦክታብርስካያ ከተባሉ የዩክሬን ከተሞች በ17 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንደሚገኝ ስፑትኒክ ኒውስ ዘግቧል፡፡
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቭሎዶሚር ዘነልሰኪ ከሰሞኑ ባደረጉት ንግግር እኛ “የሩሲያ ባሪያዎች አልነበርንም፤ ለወደፊትም አንሆንም ፤ የፑቲንን ሠራዊት እንፋለመዋለን” ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!