Fana: At a Speed of Life!

አዋሽ የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት በሜካናይዝድ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ባለሙያዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዋሽ የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት በተለያዩ የሜካናይዝድ ሙያዎችና በከባድና ቀላል መኪና አሽከርካሪነት ያሰለጠናቸውን ባለሙያዎች አስመርቀ፡፡

በዝግጅቱ ላይ የምድር ሀይል ጠቅላይ መምሪያ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀነራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን፣ የማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ተመስገን አቦሴን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊና የአካባቢው የመስተዳደር አካላት ተገኘተዋል።

በምረቃ ስነስርኣቱ ተመራቂዎች የተለያዩ የሜካናይዝድ ወታደራዊ ትዕይንቶችን ለእድምተኞች አሳይተዋል፡፡

አዋሽ የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት በሀገራችን ብቸኛው የወታደራዊ ሜካናይዝድ ማሰልጠኛ ተቋም ሲሆን÷ በምስራቅ አፍሪካ ተመራጭና ግንባር ቀደም የስልጠና ማዕከል ለመሆን በመስራት ላይ የሚገኝ ሀገራዊ ሀብት መሆኑን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.