ፋና ስብስብ

የአፍሪካ ድንቃድንቆች መዝገብ ለአለም አጭሯ ሴት እና የኢትዮጵያ ረጅሙ ወንድ እውቅና በመስጠት ስራ ጀምሯል

By Feven Bishaw

March 11, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጀመሪያው ዙር የአፍሪካ ድንቃድንቆች መዝገብ የዓለም አጭሯ ሴት የሻሌ ወርቁ  ከወላይታ እና የኢትዮጵያ ረጅሙ ወንድ ነገዎ ጅማ ከመቂ እውቅና ተሰጣቸው::

የዓለም አጭሯ ሴት ኢሻሌ ወርቁ 61 ሴ.ሜ ስትሆን የኢትዮጵያ ረጅሙ ወንድ ነገዎ ጅማ ደግሞ 2 ሜትር ከ25 ሴንቲ ሜትር መሆኑ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያውያን የተመሰረተው ይሄው የአፍሪካ ድንቃንቆች መዝገብ “ከምንም ወደ ታላቅንነት”በሚል መነሻነት የሀገሪቷን ባህል በማስተዋወቅ እና ፈጠራን በማበረታታት ጀግኖችን መፍጠር ላይ ትኩረቱን በማድረግ ነው የመጀመሪያ ስራውን እውቅና በመስጠት የጀመረው::