Fana: At a Speed of Life!

ከብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ጋር ተያይዞ የሚካሄዱ መርሃ ግብሮች ተጀምረው እስከሚጠናቀቁ ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደረጉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ጋር ተያይዞ የሚካሄዱ መርሃ ግብሮች ተጀምረው እስከሚጠናቀቁ ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደርገዋል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሄድ ሲሆን÷ ጉባኤውን ተከትሎ የሚከናወኑ ልዩ ልዩ ተግባራት ስኬታማ ሆነው እንዲጠናቀቁ ለማስቻል የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል ፡፡

ጉባኤውን ተከትሎ መጋቢት 2 ቀን እና መጋቢት 5 ቀን 2014 ዓ/ም በአዲስ አበባ ልዩ ልዩ ፕሮግሞች ይካሄዳሉ፡፡

በዚህ መሰረት መጋቢት 2 ቀን 2014 ዓ/ም ምሽት አራት ኪሉ አካባቢ የሚካሄደው ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ አራት ኪሎ የሚወስዱ መንገዶች ከፍል ውሃ ወደ ሸራተን ሆቴል፣ ጋራዥ በሸራተን ሆቴል ወደ ንግድ ማተሚያ፣ ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ኮንሰን ፣ ከአምባሳደር መናፈሻ ወደ ሸራተን ሆቴል ለተሸከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ መጋቢት 5 ቀን 2014 ዓ/ም የሚካሄደው ተመሳሳይ ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ወደ አራት ኪሎ የሚውስዱ መንገዶች ከቀበና በቤልኤር ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ ቤልኤር መብራት፣ ከስድስት ኪሎ ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ ቅድስተ ማርያም ትራፊክ መብራት፣ ከፒያሳ በሰባ ደረጃ ቅድስተ ማርያም የሚወስደው መንገድ አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ቢሮ፣ ከቴዎድሮስ አደባባይ በእሪ በከንቱ ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ እሪ በከንቱ መብራት፣ ከአዋሬ ገበያ በጥይት ቤት አራት ኪሎ የሚወስደው አዋሬ አደባባይ፣ ከኮንሰን ወደ ፓርላማ የሚወስዱት መንገዶች በተጠቀሱት ቀናት ዝግጅቶቹ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቁ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡

በመሆኑም አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትእዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.