Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ያላቸውን ግንኙነት የሚያጠናክሩበት ጊዜው አሁን ነው አሉ የደቡብ ሱዳን ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር

አዲስ አበባ፣መጋቢት 2፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ያለቸውን ግንኙነት የሚያጠናክሩበት ጊዜው አሁን ነው ሲሉ የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት እና የገዥው ፓርቲ የሱዳን ሕዝብ የነፃነት ንቅናቄ (ኤስ ፒ ኤል ኤም) ምክትል ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ዶ/ር ጀምስ ዋኒ ኢጋ ገለጹ፡፡

የኤስ ፒ ኤል ኤም ምክትል ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ዶ/ር ጀምስ ዋኒ ኢጋ በብልፅግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ መክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ፖለቲካዊ ችግር ባጋጠመን ጊዜ ያገዘችን የደቡብ ሱዳን ዋነኛ ወዳጅ ሀገር ናት፤ ኢትዮጵያ ባታግዘን ኖሮ ምን አልባትም ደቡብ ሱዳን ሀገር ላትሆን ትችል ነበር ብለዋል፡፡

ደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያን ውለታ የምትከፍለበት ጊዘው አሁን ነው፥ የኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ግንኙኘት ተጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት፡፡

የኤስ ፒ ኤል ኤም እና የብልፅግና ፓርቲ እውነተኛ አጋርነት እና ትብብር ቀጣይ እንደሚሆንም አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.