በመካሄድ ላይ ያለውን የብልፅግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ አስመልክቶ የእራት ግብዣ መርሃ ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመካሄድ ላይ ያለውን የብልፅግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ አስመልክቶ ብልፅግና ፓርቲ ያዘጋጀው የእራት መርሃ ግብር በወዳጅነት ፓርክ ተካሂዷል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ “ከፈተና ወደ ልዕልና!” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ጉባኤውን አስመልክቶ በአዲስ አበባ በወዳጅነት ፓርክ ዛሬ በተዘጋጀው የእራት መርሃ ግብር የጉባኤው ተሳታፊዎች ታድመዋል፡፡
ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚካሄደው የፓርቲው የመጀመሪያ ጉባኤ የኢትዮጵያውያንን ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያረጋግጡ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉበት ፓርቲው አስታውቋል።
ፎቶ – ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት