Fana: At a Speed of Life!

በጣርማ በር ወረዳ አሸባሪው ህወሓት ጥሎት የሄደውን የሞርታር ፊውዝ ሲነካኩ የነበሩ 2 ህጻናት ህይወታቸው አለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማ በር ወረዳ ተቀጣጣይ ነገር መንገድ ላይ አግኝተው ሲቀጠቅጡ የነበሩ ሁለት ህጻናት ህይወታቸው አለፈ፡፡
 
የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽና ሚዲያ ክፍል ሃላፊ ኮማንደር ተስፋዬ ግዛቸው እንደገለጹት፥ አሸባሪው ህወሓት አካባቢውን በወረረበት ወቅት ጥሎት የሄደውን የሞርታር ፊውዝ ሲነካኩ በመፈንዳቱ በቦታው ከነበሩት አምስት ህጻናት ውስጥ የሁለቱ ሕይወት ወዲያኑ አልፏል፡፡
 
ፍንዳታው ቀሪ ሶስት ህጻናት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱንም ኮማንደር ተስፋዬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
 
ትናንት ጉዳት የደረሰባቸው ህጻናቱ በደብረብርሃን ኮምፕሬሄሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
 
በአላዩ ገረመው
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.