Fana: At a Speed of Life!

የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ከምንም ጊዜ በላይ አበክሮ እንደሚሰራ የብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ ከምንም ጊዜ በላይ አበክሮ እንደሚሰራ የብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ።
ፓርቲው አንደኛውን ድርጅቲዊ ጉባኤው እያካሄደ ይገኛል።
የጉባኤውን ሁለተኛ ቀን ውሎ አስመልክቶ የብልጽግና ፓርቲ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ መግለጫ ሰጥተዋል።
የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት ማስጠበቅ ቅድሚያ የሚሰጡት ስራ እንደሆነ በጉባኤው ከስምምነት መደረሱን አስታውቀዋል።
ፓርቲው ከሰላም የሚያስቀድመው ነገር አለመኖሩን ነው የተመለከተው።
የፓርቲውን አደረጃጀት፣ አመራር እና አባላት አስተሳሰብ በሚገባ በመግራት ሰላምን ማስጠበቅ የብልጽግና ፓርቲ ትልቁ ፕሮጀክት ነውም ብለዋል።
አሁን የሚፈጠረው የብልጽግና አመራር የሀገሪቱን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ ፣ የደህንነት እና ማህበራዊ ችግሮች መፍታት 24 ሰዓት የሚሠራው ስራ እንደሆነም በጉባኤው ከስምምነት ተደርሷል ብለዋል ።
የትግራይ ህዝብን በተመለከተም ጉባኤው የመከረ ሲሆን፥ በአሸባሪው ህወሓት ድርጊት ሳቢያ ህዝቡ ለችግር መዳረጉን አንስቷል።
ብልጽግና ፓርቲ በትግራይ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ ለማስቀረትና እፎይ ብሎ እንዲኖር ለማስቻል አሉ የተባሉ የሰላም አማራጮችን በሙሉ እንደሚጠቀም አስታውቀዋል።
ጉባኤው ድርቅ በተደጋጋሚ በሚከሰትባቸው ቆላማ የሀገሪቱ አካባቢዎች የዜጎችን ችግር በዘላቂነት የሚፈታ ስራ መሰራት እንደሚገባም ተመልክቷል።
የፓርቲው ጉባኤ አምስት አጀንዳዎች እንዳሉትም ዶክተር ቢቂላ ገልጸዋል ።
እስካሁንም ከአጀንዳዎቹ መካከል የፓርቲውን ማዕከላዊ ኮሚቴ ሪፖርት እና የፓርቲውን የኢንስፔክሽን ዕና ስነ ምግባር ሪፖርት አድምጦ አጽድቋል ።
በዓልአዛር ታደለ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.