Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ፖሊሲና ማስፈጸሚያ ስትራቴጂ ላይ ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሰላም ፖሊሲና ማስፈጸሚያ ስትራቴጂ ላይ ከምሁራን ጋር ውይይት ተደረገ፡፡
ከ15 ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ የሰላም፣ የፌደራሊዝም እና የግጭት አስተዳደር ምሁራን በኢትዮጵያ የሰላም ፖሊሲና ማስፈፀሚያ ስትራቴጂ ላይ በአዲስ አበባ ተወያይተዋል፡፡
ውይይቱ በማስፈጸሚያ ስትራቴጂው ላይ ምሁራን ለሰላምና ብሔራዊ መግባባት መሠረት ናቸው ባሏቸው ጉዳዮች ዕውቀታቸውንና ልምዳቸውን ያካፈሉበት ነው ተብሏል፡፡
በሰላም ሚኒስቴር የስትራቴጂክ አጋርነትና ተጠሪ ተቋማት ማስተባበሪያ ዳይሬክተር ጀነራል ሻንቆ ደለለኝ÷ የኢትዮጵያ የሰላም ፖሊሲና ማስፈፀሚያ ስትራቴጂ ሰነዱ ላይ ገለፃ አድርገዋል፡፡
ምሁራኑ በቀረበው የሰላም ፖሊሲና ስትራቴጂ ሰነድ ላይ ባደረጉት ውይይት÷ የፖሊሲውን ይዘቶች መሠረት አድርገው  የሀገሪቱ ሰላም እንዲጠበቅ ይበጃሉ የሚሏቸውን ጉዳዮች በጥልቀት ማንሳታቸውም ተጠቅሷል፡፡
ማህበራዊ ሀብቶችን ለሰላም ግንባታ ጥቅም ላይ ማዋል የሚኖራቸውን በጎ ሚና መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.