የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ እና ትግራይ ህዝቦችን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ የውይይት መድረክ እየተካሄደ  ነው

By Tibebu Kebede

February 25, 2020

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ እና የትግራይ ህዝቦችን ሁለንተናዊ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በውይይት መድረኩ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶችና ታዋቂ ግለሰቦች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።