የሀገር ውስጥ ዜና

የብልፅግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ ዶክተር ዐቢይ አሕመድን የፓርቲው ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ

By ዮሐንስ ደርበው

March 12, 2022

የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ÷ “ለጉባኤው እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ ከተደመራችሁ ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች“ ብለዋል፡፡

“ክቡር አቶ አደም ፋራህ ዋና እና አጋር የሚለው ግንብ ፈርሶ ሶማሌ ከአጋርነት ወደ ብልጽግና መሪነት በተዋጽኦ ሳይሆን በብቃት የምክትል ፕሬዚዳንትነት ቦታ በማግኘታቸው እጅግ ከፍተኛ ክብር የተሰማኝ መሆኑን መግለጽ እፈልጋለሁም” ነው ያሉት።

“ኢትዮጵያዊ ሆኜ ሁላችሁንም በታማኝነት ሳላዳላ ለማገልገል እንድችል ጊዜና ሁኔታ ወደዚህ ወደዚያ እንዳይወስደኝ በጨዋነትና በትጋት ማገልገል ስለምፈልግ ጸልዩልኝም” ነው ያሉት ዶክተር ዐቢይ።

ሰብሰብ ብለን የኢትዮጵያን ትልቅነት ስናይ የሚጠይቀው ኃላፊነት ከፍተኛ ነውም ብለዋል፡፡

በሻምበል ምህረት

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ