Fana: At a Speed of Life!

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የቀብር ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የቀብር ስነ ስርዓት በቅድስት ስላሴ ካቴደራል እየተካሄደ ነው፡፡

የብፁዕነታቸው አስከሬን በቅድስት ስላሴ ካቴደራል የፀሎተ ፍትሃት፣ ስርዓተ ማህሌትና ጸሎተ ኪዳን ሲደረግለት አድሮ በአሁን ሰዓት ወደ አውደ ምህረት ወጥቶ በሊቃውንት ቤተክርስቲያን ያሬዳዊ ወረብ እየተደረገለት ይገኛል።

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የቀብር የሽኝት ስነ ስርዓት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት የበላይ አመራሮች፣ የአለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ተወካይ፣ የአፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ ተወካይ፣ የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተወካይ፣ ሊቃነ ጳጳሳት ይርህንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተወካይ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከቫቲካን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሮዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ተወካይ ተገኝተዋል።

 

የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉ ባኤ አገኘው ተሻገር፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ የአማራ ክልል ርዐሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የተለያዩ የዓለም ሀገራት አብያተ ክርስቲያናት እና በሀገር ውስጥ የሚገኙ  ኢምባሲዎችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት የሀዘን መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል።

 

 

በኃይማኖት ኢያሱ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.