የብልጽግና ፓርቲ የመጀመሪያ ጉባዔ በስኬት መጠናቀቁን ፓርቲው አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ጉባዔ በስኬት መጠናቀቁን ፓርቲው አስታወቀ፡፡
ላለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የብልፅግና አንደኛ ጉባዔ የፓርቲውን የወደፊት የትኩረት አቅጣጫ ያመላከቱ ባለስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት መጠናቀቁን ፓርቲው ገልጿል።
የኑሮ ውድነትንና የዋጋ ንረት ጊዜ ሳይሰጠው ተሰርቶበት የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል አመራሩ እና አባሉ መስራት እንዳለበት ብልጽግና ፓርቲ አቅጣጫ አስቀምጧል።
የብልጽግና ፓርቲ የህዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ በሰጡት መግለጫ እንዳብራሩት፥ ጉባኤው የዜጎችን ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያረጋግጡ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ነው የተጠናቀቀው።
የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ስርዓታዊ ማሻሻያ እንደሚያስፈልገው ያነሳው ጉባኤው፥ አመራሩ የዜጎችን ኑሮ የሚቀይሩ ስራዎችን እንዲሰራ አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል።
ጉባኤው ሀገራዊ ለውጡን ማስቀጠል፣ የዴሞክራሲ ስርዓት ማስፋት፣ ጠንካራ የዴፕሎማሲ ስራዎችን መስራት የሚያስችሉ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል ።
የብልጽግና ፓርቲ የመጀመሪያ ጉባኤ 225 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን መርጧል።
የማዕከላዊ ኮሚቴው ደግሞ 45 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን መርጧል።
ኮሚቴው የጋራ እሴቶችን የሚገነባ፣ ብዝሀነትን በአግባቡ የሚያስተናግድ ፣ ጠንካራ፣ ፍጹም ጽንፈኛ ያልሆነ ፣ ወቅታዊ ችግሮችን የሚፈታ እና ለሀገሪቱ ብልጽግና የሚተጋ አባላት ያሉት መሆኑንም ተመልክቷል።
ብልጽግና ፓርቲ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እና ለዜጎችን መረጋጋት ከምንም ጊዜ በላይ ቅድሚያ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራትም ወስኗል ።
በዓልአዛር ታደለ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!