የብልጽግና ፓርቲ ህዝባዊ አደራውን ለመወጣት የሚያስችሉ እርምጃዎች መወሰዱን አስታወቀ
በዚህም መሰረት በ108 ሺህ 258 አባላት ላይ ጥልቅ ግምገማ መደረጉን፤ በ10 ሺህ 658 አመራሮች ላይ እርምጃ መወሰዱን የፓርቲው ዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ አስታውቀዋል።
አቶ አደም ፋራህ የፖርቲውን አንደኛ ጉባኤ አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ 2 ሺህ 574 አመራሮች ከኃላፊነት መነሳታቸውን እና ሌሎች የማስተካከያ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ገልፀዋል።
በየክልሉ እታች ድረስ የተደራጀ እቅድ ተዘጋጅቶና ውይይት ተደርጎ በየአከባቢው ያሉ ችግሮች እንደሚፈቱም ነው የተገለጸው።
በበርካታ ጫናዎች ኢትዮጵያን ለማበርታት፣ ለማጽናትና ለማቆም የተሄደበት ርቀት ውጤታማ የሚባል ነበር ሲሉ የብልጽግና ፖርቲ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።
በሀይለየሱስ ስዩም
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ