Fana: At a Speed of Life!

የቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር የፊታችን አርብ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 18ኛው የዓለም የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር በሰርቪያ ዋና ከተማ ቤልግሬድ ይካሄዳል።
ውድድሩ የፊታችን አርብ ጀምሮ እሁድ የሚጠናቀቅ ሲሆን፥ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሀገራት በየሁለት ዓመቱ በሚደረገው መርሃ ግብር ላይ ይሳተፋሉ።
ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር በ1 ሺህ 500 እና በ3 ሺህ ሜትር በሁለቱም ፆታ የምትካፈል ይሆናል።
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በመድረኩ የተሳተፈችው እ.ኤ.አ በ1989 ዓ.ም በሃንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት ላይ በተደረገ ውድድር ነው።
ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ እና አትሌት መሠረት ደፋር በዓለም የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር አራት አራት ግዜ የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ አትሌቶች ናቸው፡፡
ለ18ኛ ጊዜ በሚካሄደውና ሀገራችን ለ17ኛ ጊዜ በምትሳተፍበት የቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ዛሬ ኳታር ዶሃ ገብቷል፡፡
በቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በትላንትናው እለት በቤልቪው ሆቴል አሸኛኘት እንደተደረገለት ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.