Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት የሚያደርስባቸውን ግፍ በመሸሽ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች አማራ ክልል ገቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት የሚያደርስባቸውን ግፍ እና በደል በመሸሽ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ከትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በአጎራባች የአማራ ክልል ከተሞች መጠለላቸው ተገለጸ።
የአሸባሪውን ቡድን ግፍና ጭቆና በመሸሽ በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማና አካባቢው ብቻ በሦስት መጠለያ ጣቢያዎች በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች የተጠለሉ ሲሆን÷ በመንግስት የዕለት ደራሽ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተገልጿል።
በተመሳሳይ በሰቆጣ ከተማም በርካታ የትግራይ ክልል ተፈናቀዮች ከመንግስትና ከህዝብ ድጋፍ እያገኙ ሲሆን÷ በየቀኑ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ተፈናቀዮች ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ አጎራባች የአማራ ክልል አካባቢዎች እየተሰደዱ ነው፡፡
ተፈናዮቹ የህወሓት አመራሮችና ታጣቂዎች በሕዝቡ ላይ ዘግናኝ ግፍና በደል እየፈፀሙ መሆናቸውንም ተናረዋል።
ከትግራይ ክልል የመጡ ተፈናቃዮች ለኢፕድ ሪፖርተሮች እንደገለጹት÷ ለትግራይ ሕዝብ ተብሎ ከኢትዮጵያ መንግስት የሚላከውን እርዳታ የሽብር ቡድኑ በመከልከልና ረሃቡን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለዳግም ጦርነት አስገድዶ እየመለመለበት ነው፡፡
የቆቦ ከተማ ሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሀምሳ አለቃ አበበ ደርሶ እንደተናገሩት÷ እስካሁን በቆቦ ከተማ ተጠልለው የሚገኙ ከ46 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች አሉ።
አሁንም ወደ ከተማው እየመጡ ያሉ ዜጎች ከከተማው አቅም በላይ ስለሆነና እውነተኛ ተፈናቃዮችን መርዳት እንዲቻል ተፈናቃዮቹ በሀብሩ ወረዳ ወደሚገኘው ጃራ አካባቢ ለመውሰድ ሁኔታዎች እየተመቻቹ ነው ብለዋል፡፡
ለተፈናቃዮች መጠለያ የሚሆኑ ድንኳኖች፣ የውኃ ማጠራቀሚያ ታንከሮች፣ ምግብ፣ አልባሳትና ሌሎችም መገልገያ ቁሳቁሶችም መዘጋጀታቸውን ነው የተናገሩት።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.