Fana: At a Speed of Life!

“ጉድ ኔቨር ኢትዮጵያ” እና “እንቁም ለኢትዮጵያ በኖርዌይ” የተሰኙ ድርጅቶች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ጉድ ኔቨር ኢትዮጵያ” እና “እንቁም ለኢትዮጵያ በኖርዌይ” የተሰኙ ድርጅቶች ከተለያዩ አካባቢዎች በጸጥታ መደፍረስ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ከ12 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አደረጉ፡፡
“ጉድ ኔቨር ኢትዮጵያ” የተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ ለተጠለሉ ወገኖች 9 ነጥብ 8 ሚሊየንብር ግምት ያለው የምግብ ዱቄትና ጥራጥሬ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የጉድ ኔቨር ኢትዮጵያ ፊልድ ኦፊሰር አቶ በእምነት ታረቀኝ÷ ለተፈናቃዮቹ የ9 ሚልየን 894 ሺህ 187 ብር ግምት ያለው ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸው÷ ይኸውም ለ1 ሺህ 250 አባወራዎች የሚሆን 312 ነጥብ 5 ኩንታል የዳቦ ዱቄት እና 312 ነጥብ 5 ኩንታል ባቄላ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸው ተፈናቃዮች ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ የመጠለያ ጣቢያ እንደሚገኙ ጠቁመው÷ የተፈናቃይ ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ እተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ አይደለም ማለታቸውን ከደብረ ብርሃን ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በሌላ በኩል “እንቁም ለኢትዮጵያ በኖርዌይ” የተሰኘ ድርጅት ለተፈናቀሉ ዜጎች 2 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
“እንቁም ለኢትዮጵያ በኖርዌይ” በኖርዌይ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላት ለተፈናቀሉ ዜጎች ያሰባሰበውን 2 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ለአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ማስረከቡን የድርጅቱ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወይዘሮ ኢትዮጵያ አለማየሁ ለኢዜአ ገልጸዋል።
በኦስሎ የኢትዮጵያ ማህበር አባል ወይዘሮ አበባ ባህሪሹም በበኩላቸው፥ በኖርዌይ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላት ኢትዮጵያን ባላቸው አቅም እየደገፉ እንደሚገኝና ይህ ድጋፍ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.