Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ከቻይና እና አሜሪካ አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በኢትዮጵያ ከቻይና አሜሪካ አምባሳደሮች ጋር በወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት አደረጉ።

ርዕሰ መስተዳደሩ ዶክተር ይልቃል ከፋለ በውውይቱ ላይ ባድረጉት ንግር፥ አሸባሪው የህውሓት ቡድን በአማራ ክልል ወረራ ባካሄደበት ወቅት በርካታ መሰረተ ልማቶችን ያወደመና የዘረፈ መሆኑን አስረድተዋል።

አሁን ላይ የወደሙና የተዘረፉ መሰረተ ልማቶችና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፥ የቻይና መንግስትም የቆየውን ወዳጅነትና የልማት አጋርነት አጠናክሮ በማስቀጠል በመልሶ ግንባታ ስራዎች ላይ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ርዕሰ መስተዳደሩ ጠይቀዋል።

ዶክተር ይልቃል በህወሓት አሸባሪ ቡድን ወረራ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው የቻይና ፕሮጀክቶችን መልሰው እንዲቋቋሙና ወደ ስራ እንዲገቡ የክልሉ መንግስት በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸው፥ የቻይና መንግስት ለአማራ ክልል የሚያከናውነውን ልማታዊ እንቅስቃሴ አጠናክራ እንዲቀጥልም ነው የጠየቁት፡፡

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛዎ ችዩዋን በበኩላቸው፥ ቻይና ከአማራ ክልል የመንግስት መዋቅር ጋር በቅርበትና በትብብር እየሰራች መሆኑን ጠቁመው፥ የሀገራቱ የጠበቀ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ያላቸውን እምነት መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ውይይቱ በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታና ዘላቂ ልማት ላይ ያተኮረ ሲሆን÷ በተለያዩ ስፍራዎች ጉብኝት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.