Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ቻይና ሁለተኛውን የጋራ የፖለቲካ ምክክር አካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከቻይናው ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴንግ ሊ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ወቅትም በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊ እና የጋራ በሆኑ ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል።
ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ የትብብር አጋርነታቸውን ለማጠናከር ቃል መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

በውይይቱ ወቅት በሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የሚደረጉ ውይይቶችና ተደጋጋሚ ጉብኝቶች በሀገራቱ መካከል ጠንካራ የፖለቲካ መተማመን እንዲፈጠር እንደሚያግዝ ተነስቷል።

አምባሳደር ሬድዋን በዚህ ወቅት ቻይና በፀረ ኮቪድ ዘመቻ ለኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን ድጋፍ አድንቀው፥ ኢትዮጵያ ከቻይና ኩባንያዎች ጋር በመሆን የኮቪድ-19 ክትባትን በሀገር ውስጥ የማምረት ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።

የቻይናው ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው÷ ቻይና ለኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን የኮቪድ -19 ክትባት ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቅሰው፥ የኮቪድ-19 ክትባትን ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለማዘጋጀት የሚፈልጉ ኩባንያዎቿን እንደምታበረታታ አስረድተዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.