Fana: At a Speed of Life!

የፋይናንስ ዘርፉን ማቀላጠፍ የሚያስችል “ኩፕ ቦት” የተሰኘ መተግበርያ ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የፋይናንስ ዘርፉን ለማቀላጠፍ የሚያስችል “ኩፕ ቦት” የተሰኘ መተግበርያ አበልጽጎ ዛሬ በይፋ ስራ አስጀምሯል።
መተግበሪያው ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ጋር በጋራ ለመስራት በተደረገ ስምምነት የበለጸገ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
“ኩፕ ቦት” ሰዎች በየትኛውም ቦታ የሚፈልጉትን መረጃ እና አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ታስቦ የበለጸገ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
አገልግሎቱ ደንበኞች የሂሳብ እንቅስቃሴያቸውን፣ አዲስ የባንኩ ደንበኛ ለመሆን የሚያስፈልጉ መረጃዎችን፣ ኤትኤም እና የይለፍ ቁጥሩ (ምስጢር ቁጥሩ) ቢጠፋ፣ ደንበኞች ካሉት የቋንቋ አማራጮች በተፈጥሮ ቋንቋ ጥያቄን ጽፎ በማቅረብ አልያም በዝርዝር አገልግሎት ማመላከቻ (ሜኑ)ተጠቅሞ የተፈለገውን መረጃ እና አገልግሎት ማግኘት ያስችላል ተብሏል፡፡
ለአብነት ቼክ ያለቀባቸው ደንበኞች፣ አዲስ ኤትኤም ወይም ጠፍቶባቸው ለመቀየር የፈለጉ ደንበኞች የሚያመለክቱትም ሆነ የስራው ሂደት ምን እንደደረሰ ለማወቅ በቻት ቦት አማካኝነት በተሰጣቸው የመከታተያ ቁጥር አማካኝነት መከታተል ያስችላቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ አገልግሎት የሚውል “ኩፕ ቦት” መተግበሪያን በማበልጸግ ዛሬ በይፋ ስራ አስጀምሯል።
በታሪኩ ለገሰ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.