የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍ የጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ አስታወቀ
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ በትምህርት ዘርፍ ለኢትዮጵያ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው÷የወደሙ ትምህርት ቤቶች ለመገንባት በሚደረገው ጥረትም ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
የኤጀንሲው የኢትዮጵያ ዋና ተወካይ ዶክተር ካትሱኪ ሞሪሀራ በበኩላቸው÷በፈረንጆቹ ከ2006 እስከ 2020 ከ290 ሚሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ መደረጉን ገልጸው÷በዚህም ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶችን መገንባት መቻሉን አብራርተዋል፡፡
ዋና ተወካዩ በጦርነት የወደሙና የፈራረሱ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ተቋማቸው የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደረግ ጠቁመው÷ ለትምህርት ቤቶች ከሂሳብና ሳይንስ ትምህርት ጋር በተያያዘ የሚያስፈልጉ የቤተ-ሙከራ ግብዓቶችንና ቁሳቁሶችን እንደሚያሟላ ማረጋገጣቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡