Fana: At a Speed of Life!

አገራትን በመውረር ብዙዎችን በቦምብ የገደለችው አሜሪካ ፑቲንን “የጦር ወንጀለኛ” የማለት ሞራል ሊኖራት አይችልም – የሩስያ ቃል አቀባይ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራቅን ጨምሮ የውጭ አገራትን በመውረር በዓለም ዙሪያ በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በቦምብ የገደለች አሜሪካ ፑቲንን የጦር ወንጀለኛ የማለት ሞራል የላትም ሲሉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ተናገሩ፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን “ፑቲን የጦር ወንጀለኛ ናቸው” ማለታቸውን ተከትሎ ክሬምሊን በጉዳዩ ላይ መልስ ሰጥታለች፡፡

የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ እንደተናገሩት÷ ከዩናይትድ ስቴትስ የሚሰነዘረው ይህ አይነቱ አስተያየት ተቀባይነት የሌለውና ይቅር የማይባል ነው ብለዋል።

ዲሜትሪ ፔስኮቭ አክለውም በዓለም ዙሪያ በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በቦምብ የገደለች ሀገር መሪ ፕሬዚዳንት ፑቲንን የጦር ወንጀለኛ ማለታቸው ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

ሩስያ በዩክሬን ላይ ያደረሰችውን ጥቃት ዋሽንግተን እያወገዘች ቢሆንም፥ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ፑቲንን “የጦር ወንጀለኛ“ በማለት ሲገልጹ ይህ የመጀመሪያቸው መሆኑም ተዘግቧል፡፡

የሩስያ ኃይሎች ያለአንዳች ጥንቃቄ በዩክሬን ከተሞች ላይ በማነጣጠር ጉዳት እያደረሉ ነው የሚለውን የአሜሪካ ወቀሳ አስመልክቶ ፕሬዚዳንት ፑቲን በሰጡት ምላሽ፥ የሩስያ ጦር የተሰጣቸውን ዒላማዎች በትክክል መፈጸም የሚችሉ ዘመናዊ የጦር መሳሪዎችን የታጠቀ እና ወታደራዊ ዒላማዎችን ብቻ ነጥሎ የሚመታና የሚያጠቃ ሠራዊት እንደሆነ መግለጻቸውን የአር ቲ ዘገባ አስታውሷል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.