የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር በጅማ ከተማ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በጅማ ከተማ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡
ሚኒስትሯ ምዕራፍ ሁለት የአዌቱ የወንዝ ዳር ልማትና ሌሎች ፕሮጀክቶችን የጎበኙ ሲሆን፥ ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የከተማው አስተዳደር እያደረገ ያለው ክትትልና ቁጥጥር የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።
የአዌቱ ወንዝ በከተማው ነዋሪዎች ላይ ሲያደርስ የነበረውን ጉዳት በቅርበት አውቃለሁ ያሉት ሚኒስትሯ፥ አሁን እየተሰራ ያለው ፕሮጀክት ችግሩን ከመሰረቱ እንደሚፈታ ተናግረዋል።
በሌሎች ከተሞችም የህብረተሰቡን ችግሮች ከመሰረቱ የሚፈቱ ፕሮጀከቶች ላይ ትኩት ተደርጎ እንደሚሰራ ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።
የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ነጂብ ራያ በበኩላቸው፥ ፕሮጀክቱ በቀጣይ ሁለት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ብለዋል።
በሙክታር ጣሃ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!