Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የሥነ ምግባር ጉድለት ያሳዩ 146 የፖሊስ አመራሮችና አባላት ከሥራ ተሰናበቱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሥነ ምግባራቸው ፖሊስን የማይመጥኑና ጥፋት አጥፍተዋል ያላቸውን 146 የፖሊስ አመራሮችና አባላት ከሥራ ማሰናበቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ባለፉት 6 ወራት ያከናወናቸውን የወንጀል መከላከልና ምርምራ ተግባራትን አፈፃፀም አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ፥ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በርካታ ተግባራት እንደተከናወኑ ተናግረዋል።

በተደረገ ፍተሻና ብርበራም 47 ቦምብ፣ ስምንት ፈንጂዎች፣ 113 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 422 ልዩ ልዩ ሽጉጦች ከ17 ሺህ በላይ የክላሽ፣ ከ8 ሺህ በላይ የሽጉጥ ጥይቶች፣ 2 ሺህ 901 የብሬን እና ስምንት የመትርየስ እና 183 የልዩ ልዩ የጦር መሳሪዎች ጥይቶችን መያዝ እንደተቻለም ገልጸዋል፡፡

ከእነዚህ የጦር መሳሪያዎች በተጨማሪ 57 የጦር መሳሪያ መነፅር፣ 2 የጦር መሳሪያ ኮምፓስ፣ 64 ወታደራዊ የመገናኛ ሬድዮ፣ 3 የመገናኛ ሬዲዩ ቻርጀር፣ 6 ጂፒኤስ እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁስ ከእነተጠርጣሪዎቹ ተይዘው አስፈላጊው ምርመራ ሥራ እየተሰራ እንደሆነ ተነስቷል፡፡

ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውሩን የመከለከልና ህገ-ወጦችን ለህግ የማቅረቡ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን ከአስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.