የአግሮ ኢንዱስትሪ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር አሽናፊዎች ተሸለሙ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምስቱ የዩኒቨርሲቲ የአግሮ ኢንዱስትሪ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር አሽናፊዎች ተሸለሙ፡፡
ሽልማቱን ያበረከቱት የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን÷ የአገራችን የጀርባ አጥንት የሆነውን እና ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በዓመት 44 ከመቶ ሥራ ለመፍጠር የሚያቅድበት የግብርና ዘርፍ መሆኑን ገልጸው የአርሶ አደሩን ሕይወት ለማቃለል ያለመ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር መካሄዱን አድንቀዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲዎች የቀለም ብቻ ሳይሆኑ ዕውቀት እና አመለካከት የሚቀረጽባቸው እንደመሆናቸው÷ የወጣቶቹ ሃሳቦች ወደሥራ እንዲያድጉ በማሰልጠን እና በመደገፍ ላይ ያሉትን እያበረታታን ሌሎችም የእነሱን ፈለግ እንዲከተሉ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
አምስቱ ቡድኖች እያንዳንዳቸው ብር 230ሺህ የሥራ ማስጀመሪያ ገንዘብ እና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ከተረፈ ምርት ማዳበሪያ ያመረቱ ፣ ከቀርከሃ ብስክሌት የሠሩ፣ የእንስሣት መኖ ከተረፈ ምርቶች ያዘጋጁ፣ ከቡና ቅጠል በዘመናዊ መልክ ሻይ ቅጠል ያመረቱ እና ከእንሰት ስታርች እና የተለያዩ ምግቦችን ያቀረቡ የአግሮ ኢንዱስትሪ የፈጠራ ሃሳቦች ናቸው አሸናፊ የሆኑት መባሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!