Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀና ተሰናባቹ የሳዑዲ አምባሳደር በሀገሪቱ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሁኔታ ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ተሰናባቹ በኢትዮጵያ የሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር ሳሚ ጃሚል አብዱላህ በሀገሪቱ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሁኔታ ላይ መከሩ፡፡

በውይይታቸውም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደሩ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር በመስራታቸው ምስጋና አቅርበዋል።

ሁለቱ ወገኖች በሳዑዲ አረቢያ ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሁኔታ የመከሩ ሲሆን ፥ ከስደት ተመላሽ ዜጎችን የመመለሻ እና የማገገሚያ መርሃ ግብሮችን በተመለከተ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።

አምባሳደር ሳሚ ጀሚል አብዱላህ በበኩላቸው ፥ በኢትዮጵያ ባደረጉት የሶስት ዓመት የስራ ቆይታ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ላደረጉላቸው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።

አምባሳደሩ አክለውም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወደፊት ለሚያደርጉት ጥረትና መልካም ምኞት ማመስገናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.