Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮምን በከፊል ወደግል የማዛወር እቅድ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 9፣2014 (ኤፍ ቢሲ) መንግስት ኢትዮ ቴሌኮምን በከፊል ወደግል የማዛወር እቅዱን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፉን አስታወቀ፡፡የገንዘብ ሚኒስቴር በላከው መግለጫ በዓለም ላይ እና በሃገር ውስጥ ማክሮ ኢኮኖሚ ላይ የሚታየውን ፈጣን ለውጥ በማጤን ተቋሙን በከፊል ወደ ግል የማዛወር እቅድ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ መወሰኑን አስታውቋል።

ውሳኔውም ለሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ለኢትዮጵያ ህዝብ የተሻለ ጥቅም እንደሚሰጥ እንደታመነበት ነው በመግለጫው የተመላከተው፡፡

መንግስት ባለፈው አመት መስከረም ወር ላይ የኢትዮ ቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ ለግሉ ዘርፍ ለመሸጥ ማቀዱ ይታወሳል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም መንግስት ፍላጎት ካሳዩ አካላት ጋር ውይይት ማድረጉም የሚታወስ ነው።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.