Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርብ 30 ሺህ ቶን ቡና ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው የምርት ዘመን ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርብ 30 ሺህ ቶን ቡና መሰብሰቡን በጋምቤላ ክልል የማጃንግ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት መምሪያ ገለጸ።

በመምሪያው የቡና ሻይ ቅመማ ቅመም ቡድን መሪ አቶ ሲሳይ በላይነህ÷በዘንድሮው አመት የዞኑ የቡና ምርት አያያዝ ከፍተኛ በመሆኑ 38 ሺህ ቶን ለማዕከላዊ ገበያ ይቀርባል ተብሎ እንደሚገመት ነው የገለፁት፡፡

ባለፈው ዓመት ከነበረው 16 ሺህ ቶን የቡና ምርት ጋር ሲነፃፀርም የዘንድሮው የ14 ሺህ ቶን ቡና ብልጫ እንዳሳየም ተናግረዋል።

በአብዱ ሙሃመድ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.