Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በህገ-ወጥ መልኩ የተለያዩ የውጭ ሃገራት ገንዘቦችን ሲመነዝሩ የነበሩ 7 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦሌ ክፍለ ከተማ በሞባይል ስልክ መሸጫ እና በሸቀጣ ሸቀጥ መደብር ውስጥ በህገ-ወጥ መልኩ የተለያዩ የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን ሲመነዝሩ የነበሩ ሰባት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለጸ፡፡
ፖሊስ መጋቢት 8 ቀን 2014 ዓ.ም በቦሌ ክ /ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሸገር ህንፃ ማክ ሞባይል ስልክ መሸጫ እና ወረዳ 4 ልዩ ቦታው አውራሪስ ሆቴል አካባቢ በሚገኝ የሸቀጣ ሸቀጥ መሸጫ ሱቆች ላይ ፖሊስ ባደረገው ፍተሻ በርካታ ገንዘቦች መያዙን አስታውቋል፡፡
የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ በጥናት ላይ ተመስርቶ በህግ አግባብ ባከናወነው ብርበራ ከሁለቱም ሱቆች በአጠቃላይ ከ762 ሺህ በላይ የኢትዮጵያ ብር፣ 19 ሺህ 65 የአሜሪካ ዶላር፣ 17ሺህ 750 ዩሮ፣ 40 የእንግሊዝ ፓውንድ፣ 3 ሺህ 800 የካናዳ ዶላር ተገኝቷል፡፡
በተጨማሪም የሩሲያ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች፣የፈረንሳይ፣ የአውስትራሊያ፣ የኤርትራ ፣ የሱዳን፣ የስዊድን ፣የቻይና ፣ የባህሬን እና የኳታር መገበያያ ገንዘቦች በኤግዚቢትነት መያዛቸው ነው የተገለጸው፡፡
በወንጀሉ የተጠረጠሩ 7 ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ህብረተሰቡም ማንኛውም ሰው ተመሳሳይ ተግባር የሚፈፅሙ ህገ-ወጦችን በሚመለከትበት ወቅት ለጸጥታ አካላት ጥቆማ መስጠቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.