Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ዘይት እየተሰራጨ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ዘይት እየተሰራጨ ነው፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በልደታ፣ ቂርቆስ እና ቦሌ ክፍለ ከተሞች ዘይት እየተሰራጨ መሆኑን በቅኝቱ ተመልክቷል።

ሸማቾች ÷ዘይት እየቀረበ ቢሆንም ለሁሉም እየተዳረሰ አይደለም፤ የአቅርቦት እና ፍላጎት የተጣጣመ አይደለም ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በየክፍለ ከተሞቹ ዘይት እየተከፋፈለ ያለው በኩፖን ሲሆን÷ በቀጣይ ለመንግስት ሰራተኞች ይቀርባል ነው የተባለው።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አደም ኑር÷ የዘይት እጥረት ከተከሰተ ወዲህ 1 ሚሊየን 459 ሺህ ሊትር ዘይት ተሰሯጭቷል ብለዋል።

የተደራሽነት ችግር ባለባቸው አከባቢዎች ከሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በተጨማሪ በተመረጡ ቸርቻሪ ሱቆች እናቀርባለን ብለዋል ሃላፊው።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የዘይት አቅርቦት እና ፍላጎት ለማመጣጣም ትኩረት እሰጣለሁ ብሏል።

በአልማዝ መኮንን

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.