Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

 አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው።

የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ባንቻየሁ ድንገታ ጉባኤውን በንግግር ሲከፍቱ፥ የምክር ቤቱ አባላት ለመልካም አስተዳደር፣ ልማት፣ ፍትህ መረጋገጥ ኃላፊነታቸውን በትጋት ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

በቀጣይም የግንባታ ፕሮጀክቶች ጥራት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሻሻል፣ የወጣቶችና የሴቶች የስራ እድል ፈጠራ እንዲጠናከር፣ የብሄራዊ መግባባቱ ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተለይም የምክር ቤት አባላት ሚናቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የኑሮ ውድነቱን በማቃለልና የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉም አካላት ተቀናጅተው እንዲንቀሳቀሱ አፈ ጉባኤዋ ጥሪ አቅርበዋል። በጉባዔው የክልሉ መንግስት የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።

ምክር ቤቱ በልዩ ልዩ ረቂቅ አዋጆችና ሹመት ላይ በመምከር ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ መንግስት ፕሬስ ሴክሬታርያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.