Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ለደቡብ ሱዳን የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች-አምባሳደር ነቢል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ለደቡብ ሱዳን የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ነቢል ማህዲ ገለጹ፡
 
አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ኤልዛቤት አቺዩ ዮል ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም ሁለቱ አገራት በጤናው ዘርፍ እያደረጉት ስላለው ትብብር ዙሪያ መክረዋል፡፡
 
አምባሳደር ነቢል ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ከደቡብ ሱዳን የተቀበለቻቸውን 29 የስፔሻላይዜሽን ባለሙያዎች ማሰልጠን ጨምሮ በዘርፉ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠውላቸዋል።
 
አርመን ሀንሰን የተባለው የምርምር ተቋም በወባና ሌሎች የተዘነጉ ትሮፒካል በሽታዎች ዙሪያ ከደቡብ ሱዳን አቻ ተቋም ጋር በትብብር ለመስራት የያዘውን ዕቅድ ለሚኒስትሯ አብራርተዋል።
 
የደቡብ ሱዳን ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ኤልዛቤት አቺዩ ዮል በበኩላቸው÷ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን የነጻነት ትግል ጀምሮ እስካሁን እያደረገች ላለችው ያልተቋረጠ ድጋፍ አመስግነው÷ድጋፏን አጠናክራ እንድትቀጥልም ጠይቀዋል፡፡
 
በጤናው ዘርፍ ያለውን የሰው ሃብት አቅም ለማሳደግ ኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን ድጋፍ ማድነቃቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስጼር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.