Fana: At a Speed of Life!

ጨፌ ኦሮሚያ ከነገ ጀምሮ መደበኛ ጉባኤውን ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጨፌ ኦሮሚያ ከነገ ጀምሮ መደበኛ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ሰዓዳ አብዱራህማን ገለጹ፡፡
አፈ ጉባኤዋ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ÷ ጉባኤው በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር፣ ህዝብን ለከፍተኛ ምሬት እየዳረገ የሚገኘው የኑሮ ውድነት እና በአገልግሎት አሰጣጡ በሚታዩ ጉድለቶች፣ በስራ እድል ፈጠራ ላይ ያሉ አበረታችና መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ፣ በህግ የበላይነት፣ በህዝብ ሰላም እና ደህንነት እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ላይ ጉባኤው አቅጣጫ ያስቀምጣል ብለዋል፡፡
ለሁለት ቀናት የሚቆየው ጉባኤው በተለያዩ ረቂቅ አዋጆችና ደምቦች ላይ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ እና የተለያዩ ሹመቶችንም እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡
በአፈወርቅ አለሙ፣ ዳግማዊ ዴክሲሳ እና ገመቺስ ታሪኩ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.