Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ለሰላም፥ለመልካም አስተዳደርና ለልማት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል መንግስትና ህዝብ የሀገር ሉዓላዊነት እና ሰላም ከማስከበር ጎን ለጎን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ የልማት ስራዎችን ለማፋጠን በልዩ ትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ባለፋት ሰባት ወራት የተከናወኑ የክልሉን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት፥ ለሁለት ቀናት በሚቆየው የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤ በማቅረብ ላይ ናቸው።

ሽብርተኞቹ የኦነግ ሸኔ: አባ ቶርቤ እና የህወሓት ቡድን አባላት ክልሉን የጦርነት አውድማ ለማድረግ እና የልማት ስራዎችን ወደ ኋላ ለመመለስ ያደረጉትን ያልተቋረጠ እንቅስቃሴ ለመመከት መሰራቱንም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።

አሁንም እነዚህ የታጠቁ ኃይሎች በክልሉ የተለያዩ ዞኖች እየፈጸሙ ያሉትን ከፍተኛ ውድመት መከላከል ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም ነው ያሉት።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.