ዓለምአቀፋዊ ዜና

አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ ከተመድ የኢትዮጵያ ሰብአዊ ጉዳዮች የሥራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

March 21, 2022

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 12 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ ዑመር ከተመድ የኢትዮጵያ ሰብአዊ እርዳታ ሃላፊ ዶር ካትሪን ሱዚ የተመራ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልዑካን ቡድን ከክልሉ መንግስት ጋር በዘላቂ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ የሁለትዮሽ ስምምነት የተፈረመ ሲሆን፥ በክልሉ የተከሰተው ድርቅ በህብረተሰቡ ህይወት ላይ ካደረሰው ተፅዕኖ መልሶ ለማቋቋምና ዘላቂ የልማት መርሃ ግብሮችን ለመተግበር የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን በማቀድና በመተግበር ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል።

በመጨረሻም በክልሉ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን ድርቅ ለመከላከል የአምስት ዓመታት የልማት ፕሮጀክቶች ስምምነት በመፈራረም ውይይቱ መጠናቀቁን የሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!