Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የንግዱ ዘርፍ ላይ ሙስና እና ብልሹ አሰራር እየተባባሰ መምጣቱ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የንግዱ ዘርፍ ላይ ሙስና እና ብልሹ አሰራር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የፌደራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ገለጸ።

ኮሚሽኑ ”የንግድ ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ ማነቆ የወለደው ሙስና እና ብልሹ አሰራር” በሚል መሪ ሃሳብ ከተለያዩ የዘርፉ ተዋናዮች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በመድረኩ በዚሁ ዙሪያ የቀረበው የውይይት መነሻ ፅሁፍ በኢትዮጵያ የንግድ ዘርፍ ላይ ሙስና እና ብልሹ አሰራር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን አመላክቷል።

ለችግሩ መባባስም በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚው የሚስተዋሉ የግልጽነትና የአሰራር ብልሹነት ችግር እንዲሁም የተቋማዊ አሰራር ግድፈቶች መሆኑ ተገልጿል።

የፌደራል የሥነ ምግባርና የፀረ- ሙስና ኮሚሽነር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ፤ ከንግዱ ዘርፍ ጋር የተያያዙ ብልሹና ህገ ወጥ የአሰራር ችግሮችን ለመፍታት የተቀናጀ ጥረት የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል።
የዛሬው ውይይትም የችግሩን ስፋትና ውስብስብነት በመገንዘብ የጋራ መፍትሄ ለማበጀት የተካሄደ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ የንግድ ዘርፍ ላይ ሙስና እና ብልሹ አሰራር አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የተናገሩት ኮሚሽነሩ በዚህ ወንጀል ውስጥ የሚሳተፉትን በጥንቃቄ በመለየት የህግ ተጠያቂ የማድረግ ስራ ይከናወናል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የድሬዳዋ ንግድ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አሚኑ ጠሃ÷ የግብይት እንቃስቃሴዎች ውስጥ ያለውን ማነቆ ለመፍታት ሁላችንም መታገል ይኖርብናል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ማህበር ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ዘሀራ መሀመድ በበኩላቸው÷ የንግድ ብልሽቱ ሁላችንንም የሚጎዳ በመሆኑ ህጋዊና ፍትሃዊ የንግድ ሰንሰለት እንዲኖር በጋራ መስራት አለብን ብለዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.