Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ሊያ ከዓለም ባንክ የአፍሪካ ዋና ዳይሬክተር ጋር የጤናውን ዘርፍ ማጠናከር በሚቻልበት ውኔታ ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከዓለም ባንክ የፍሪካ ዋና ዳይሬክተር ታውፊላ ኒያማዛቦ ጋር የጤናውን ዘርፍ ማጠናከር በሚቻልበት ውኔታ ላይ ተወያዩ፡፡
 
በውይይታቸውም በሁለቱ ተቋማት መካከል የነበረው የረጅም ጊዜ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
 
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል እና ሌሎች አሽቸኳይ ምላሽ እና በዘርፉ የሚታዩ ተግዳሮቶችን መወጣት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል፡፡
 
በተለይም የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን እና የእናቶች እና ህጻናት ህክምና እንዲሁም የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ መገንባት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ መምከራቸውን ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
 
ዓለም ባንክ በጤናው ዘርፍ ለሚያደርገው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እና አጋርነትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.