Fana: At a Speed of Life!

ለሰላምና ልማት በአንድነት ከሰራን የማንሻገረው ተግዳሮት የለም- ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ

አዲስ አበባ፣ መጋት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሕዝባችን ሰላም እና ልማት በአንድነት እና በቁርጠኝነት ከሠራን የማንሻገረው ተግዳሮት የለም ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ተናገሩ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን ያሉት በመካሄድ ላይ በሚገኘው 6ኛው የክልሉ ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ለምክር ቤቱ አባላት የ6ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡
በቀረበው ሪፖርት አሸባሪው ህወሓት ያደረሰውን ወረራ እና ጥቃት ከመመከት ጎን ለጎን በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካዊ ዘርፎች ውጤት ለማስመዝገብ ጥረቶች መደረጋቸው ተመላክቷል፡፡
አሸባሪው ህወሓት በክልሉ በፈፀመው ወረራና ጥቃት በንፁሀን እንዲሁም በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል፡፡
በተለይም በህፃናት፣ በሴቶች እና አረጋውያን ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳትና መፈናቀል መድረሱን ሪፖርቱ ያመላከተ ሲሆን÷ በተመሳሳይ ከግለሰብ እስከ ድርጅቶች በንብረት ላይ ስርቆትና ከፍተኛ ውድመት መድረሱም ተብራርቷል፡፡
የክልሉ መንግስት ከመላው ሕዝብና አናብስት የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመተባበር ለመመከት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።

በአሸባሪው ወረራና ጥቃት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ የምግብ፣ የቁሳቁስ እና የህክምና አገልግሎት ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑም በሪፖርቱ ተነስቷል፡፡

በልማት ዘርፉም እንደ ሀገር የተጀመረውን የቆላማ ስንዴ ልማት አስመልክተው በክልሉ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ጠቁመው÷ በቀጣይም ሌሎች የልማት ዘርፎችን በመጨመር በስፋት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.