Fana: At a Speed of Life!

በሀገር ውስጥ የዘይት አምራቾች ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያዘጋጀው በሀገር ውስጥ የዘይት አምራቾች ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ያተኮረ ውይይት በመካሄድ ላይ ነው።

በውይይቱ የሀገር ውስጥ ዘይት አምራች ኩባንያዎችና ከዘይት ምርት ጋር ተያያዥነት ያላቸው የመንግስት ተቋማት ተገኝተዋል።

በመድረኩ በኢትዮጵያ ዘይትን አጣርተው ማምረት የሚችሉ 30 ፋብሪካዎች መኖራቸውና በሙሉ አቅማቸው ቢያመርቱ 98 በመቶ የሀገር ውስጥ ፍጆታን መሸፈን እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች እየሸፈኑ ያሉት 40 በመቶ ያህሉን ብቻ መሆኑ ተነስቷል፡፡

የፊቢላና ሪች ላንድ ዘይት ፋብሪካዎች የፋይናንስ አቅርቦት ችግር፣ የሀይል አቅርቦት መቆራረጥና አነስተኛነት፣ የግብአት እጥረትና መሰል ችግሮች የአቅማቸውን ያህል እንዳያመርቱ ማድረጉን ጠቅሰዋል።

በጥሬ እቃነት የሚያገለግሉ ምርቶች የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ሳይሸፍኑ ወደ ውጭ እየተላኩ መሆናቸውም ተጠሟል።

ከውጭ ለሚገባ የዘይት ድፍድፍ እስከ 1 ቢሊየን ዶላር በአመት እንደሚያስፈልግ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ተወካይ ተናግረዋል።

ለቅባት እህሎች ምርት ትኩረት አለመስጠት፣ የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት ችግር፣ የእሴት ሰንሰለቱ አለመጠናከር፣ ዓለማቀፋዊ ሁኔታዎች በችግርነት የቀረቡ ሲሆን ÷ባለድርሻ አካላት ምላሽ እየሰጡ ነው።

በሀገር ውስጥ ገበያ የዘይት ምርት እጥረት በመከሰቱና ዋጋው በማሻቀቡ ህብረተሰቡ ክፉኛ መቸገሩ የሚታወቅ ነው።

መንግስት የተፈጠረውን የዋጋ ጭማሪ ለማረጋጋት በማሰብ ሰሞኑን ከ12 ሚለየን ሊትር በላይ የዘይት ምርት ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት እያሰራጨ እንደሚገኝ መግለፁም የሚታወቅ ነው።

 

ብዙ ጥያቄዎች የተነሱበት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በውይይቱ ተወካይ እንደሚልክ ቢያረጋግጥም ተወካዩ ከውይይቱ ቀርተዋል።

በአፈወርቅ እያዩና በኃይለየሱስ ስዩም

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.